የተሽከርካሪ መረጃ እና የተሽከርካሪ ባለቤት መረጃ ሪፖርት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን
ለክቡራን ተገልጋዮቻችን፤
ማገልገል ክብር ነው! እኛም እናንተን ዝቅ ብለን ስናገለግል ታላቅ ደስታና ክብር ይሰማናል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎችና ስታንዳርዶች ያለምንም ችግር የማግኘት መብት ያላችሁ ሲሆን በዚህ ሰነድ የተቀመጡትን አገልግሎቶች ለማግኘት ምንም እንቅፋት ቢገጥማችሁ ችግራችሁን ለመፍታትና ችግሩን የፈጠሩ አካላትን በአሰራርና በህግ አግባብ ለመጠየቅ ዝግጁ መሆናችንን እንዲሁም ሁልጊዜም እናንተን ለማገልገል በራችን ክፍት መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን፡፡
ማገልገል ክብር ነው!
ራዕይ (Vision)
ብቁ አሽከርካሪ እና ብቃቱ የተረጋገጠ ተሽከርካሪ እንዲኖር በማድረግ በ2023 ዓ/ም ተቋሙን የሀገራችን ሞዴል አገልግሎት ሰጪ ተቋም ሆኖ ማየት፤
ተልዕኮ (Mission)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ተቋማትን በማደራጀት፣ የክትትልና ቁጥጥር አግባብን በማጠናከር፣ አፋጻጸማቸውን በማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን የመረጃ አያያዝን በማዘመን እንዲሁም ጥናትና ምርምርን በማካሄድ ውጤታማ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ብቃት ማረጋገጥ፡፡
የተቋሙ እሴቶች (Values)
- ቅንነት (Integrity)
- ግልፅነት (Transparency)
- ተጠያቂነት (Accountability)
- አለማዳለት (Impartiality)
- ቅልጥፍናና ውጤታማነት (Efficiency and Effectiveness)
- ቅንጅትና ትብብር (Integration and Collaboration)